መዝሙር 131:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን አሳረፍኋት፥ የእናቱንም ጡት እንዳስተዉት ሕጻን ዝም አሰኘኋት፥ ነፍሴ የእናቱን ጡት እንዳስተዉት በእኔ ውስጥ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ጡት የተወ ሕፃን በእናቱ ደረት ላይ እንደሚለጠፍ እኔም ዝምተኛና ጸጥተኛ ሆንኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር እንደ ማለ፥ ለያዕቆብም አምላክ እንደ ተሳለ፦ |
የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም፤
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደ ጣለህ እነሆ፤ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፣ ‘እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።
ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተመራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር በረታ።