Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 24:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደ ጣለህ እነሆ፤ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፣ ‘እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ሰዎች፥ ‘እነሆ፤ ዳዊት ክፉ ነገር ሊያደርግብህ ይፈልጋል’ ሲሉ ለምን ትቀበላቸዋለህ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እነሆ፥ ዳዊት ክፉ ነገር ይሻ​ብ​ሃል የሚ​ሉ​ህን ሰዎች ቃል ለምን ትሰ​ማ​ለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዓይንህ አይታለች፥ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተንገሩኝ፥ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 24:10
10 Referencias Cruzadas  

“የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”


ጻድቃን እጃቸውን ለክፋት እንዳያነሡ፣ የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም።


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣ በደልም በእጄ ከተገኘ፣


በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣


ሆኖም እግዚአብሔር ፈቅዶ ሰውየው ሳያውቅ በድንገት አድርጎት ከሆነ፣ እኔ ወደምወስነው ስፍራ ይሽሽ።


ደምን ለማፍሰስ ወሬ የሚያቀብሉ በውስጥሽ አሉ፤ በኰረብታ ቤተ ጣዖት የተሠዋውን የሚበሉና ዝሙትን የሚፈጽሙ ሰዎች በመካከልሽ ይገኛሉ።


“ ‘በሕዝብህ መካከል ሐሜት አትንዛ። “ ‘የባልንጀራህን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፣ “እግዚአብሔር፣ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቈርጦ ወሰደ።


ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ሰዎች፣ ‘እነሆ፤ ዳዊት ክፉ ነገር ሊያደርግብህ ይፈልጋል’ ሲሉ ለምን ትቀበላቸዋለህ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos