ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ ከተማ ሆና ተሠርታለች።
ኢየሩሳሌምስ እርስ በርስዋ እንደ ተገጠገጠች ከተማ ተሠርታለች።
ኢየሩሳሌም እርስ በርስዋ ተጠጋግታና ተጠናክራ የተሠራች ከተማ ናት።
ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤ ስድብን እጅግ ጠግበናልና፤
ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባት።
ሕዝቡ ከልቡ ስለሚሠራ፣ ቅጥሩን እኩሌታው ድረስ መልሰን ሠራነው።
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።