አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤
መዝሙር 116:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕያዋን አገር በጌታ ፊት እሄዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሕያዋን በሚገኙበት በእግዚአብሔር ፊት እኖራለሁ። |
አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤
እግዚአብሔርም፣ ‘ዘሮችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፣ እንዲሁም በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም ነፍሳቸው በታማኝነት በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አላሳጣህም’ ሲል የሰጠኝን ተስፋ ይፈጽምልኛል።
“አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ልጆችህ አንተ እንደ አደረግኸው ሁሉ በሚያደርጉት ሁሉ በጥንቃቄ በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አታጣም’ ብለህ የሰጠኸውን ተስፋ አጽናለት።
“አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በልበ ቅንነትና በትክክለኛነት በፊቴ ብትሄድ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ ሥርዐቶቼንና ሕጎቼን ብትጠብቅ፣