መዝሙር 113:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የጌታ ስም ይመስገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደኋላው ተመለሰ። |
“ለጻድቁ ክብር ይሁን” የሚል ዝማሬ፣ ከምድር ዳርቻ ሰማን። እኔ ግን፣ “ከሳሁ፤ መነመንሁ፤ ወዮልኝ! ከዳተኞች አሳልፈው ሰጡ፤ ከዳተኞች በክሕደታቸው አሳልፈው ሰጡ” አልሁ።
ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤ በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣ እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”