ምሳሌ 8:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤ እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ። |
ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ፤ ምናልባትም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
ይሁን እንጂ፣ “ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል” ደግሞም፣ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል።
ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
“ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤ እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ ሥራም ሁሉ በርሱ ይመዘናል።