ምሳሌ 7:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚጣደፍ፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ። |
ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።