በርግጥ ኤዶምን ድል አድርገሃል፤ ልብህ በትዕቢት ተወጥሯል። ክብርህን ጠብቀህ ዐርፈህ በቤትህ ተቀመጥ! ጠብ በመጫር በራስህና በይሁዳ ላይ ውድቀት ለማምጣት ችግር የምትፈጥረው ለምንድን ነው?”
ምሳሌ 3:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም ጕዳት ሳያደርስብህ፣ ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ክፉ ካልሠራብህ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም በደል ያላደረሰብህን ሰው ያለ ምክንያት አትክሰሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በላይህ የሠራው ክፉ ነገር ከሌለ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ። |
በርግጥ ኤዶምን ድል አድርገሃል፤ ልብህ በትዕቢት ተወጥሯል። ክብርህን ጠብቀህ ዐርፈህ በቤትህ ተቀመጥ! ጠብ በመጫር በራስህና በይሁዳ ላይ ውድቀት ለማምጣት ችግር የምትፈጥረው ለምንድን ነው?”