ምሳሌ 14:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂል ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝን የገዛ ንግግሩ ያስቀጣዋል፤ ጥበበኞችን ግን መልካም አነጋገራቸው ይጠብቃቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። |
ነፍሴ በአንበሶች ተከብባለች፤ በሚዘነጣጥሉ አራዊት መካከል ወድቄአለሁ፤ እነዚህም፣ ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፣ ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሰዎች ናቸው።
ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት ዐሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለ ተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለ በለጠው የሰው ዐይኖች የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለ ነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ።
በትዕግሥት እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ፣ እኔ ደግሞ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
“ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤ እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ ሥራም ሁሉ በርሱ ይመዘናል።