ምሳሌ 13:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፥ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ ሲዘገይ ልብን ያሳዝናል፤ የተመኙት ነገር ሲፈጸም ግን ደስ ያሰኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት። |
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።
ወንዙም በከተማዪቱ አውራ መንገድ መካከል ይፈስስ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ጊዜ ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ሕዝቦች የሚፈወሱባቸው ነበሩ።