ምሳሌ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ግን እግዚአብሔር ይፈርድበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥ ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፤ ክፉ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ግን እርሱ ይፈርድባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል። ዐመፀኛ ሰው ግን ቸል ይባላል። |
ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።