ዘኍል 8:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሌዋውያን ላይ ይህ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል፤ ዕድሚያቸው ሀያ አምስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ያሉት የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኻያ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሌዋዊ ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቱን ይፈጽማል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሀያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። |
በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።”
ለመሆኑ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? መንጋ እየጠበቀ የከብቱን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ፤ አስቀድሞ ስለ አንተ በተነገረው ትንቢት መሠረት ይህን ትእዛዝ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም እርሱን በመከተል መልካሙን ገድል እንድትጋደል ነው።