Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 8:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ኻያ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሌዋዊ ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቱን ይፈጽማል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “በሌዋውያን ላይ ይህ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል፤ ዕድሚያቸው ሀያ አምስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ያሉት የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “የሌ​ዋ​ው​ያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሀያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 8:24
16 Referencias Cruzadas  

ዕድሜአቸው ሠላሳና ከዚያም በላይ የሆኑትን ሌዋውያን ወንዶችን ቈጠረ፤ ጠቅላላ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ሆነ፤


በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ የሚደርሰውን ወንዶች ሁሉ መዝግብ።


የጦር መሣሪያዎቻችንም ምሽግ ለማፍረስ የሚያስችል መለኮታዊ ኀይል ያላቸው ናቸው እንጂ ዓለማዊ የጦር መሣሪያዎች አይደሉም።


ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?


በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠር፤


የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሚከተለውን ትእዛዝ በዐደራ እሰጥሃለሁ፤ ትንቢቱን በመከተል መልካም ጦርነትን ተዋጋ፤


ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠር፤


በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል መግባት የቻሉ፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሚሆን ሁሉ


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦


ኀምሳ ዓመት ሲሞላላቸው የአገልግሎት ሥራቸውን ይተዋሉ፤ ከዚያም በኋላ አይሠሩም።


የካህናት ሥራ ምድብ በጐሣ በጐሣ ሲሆን፥ ዕድሜአቸው ኻያ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን፥ የሥራ ምድብ ግን በሚያከናውኑት የሥራ ዐይነት የሚወሰን ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios