በሰይፋችሁ ትመካላችሁ፤ አስጸያፊ ነገሮችን ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት ታረክሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?’
ዘኍል 5:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ የቅናት ሕግ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በትዳር ላይ እያለች ወደ ሌላ ሄዳ ከረከሰች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሚስት በባልዋ ሥልጣን ሥር እያለች እርሱን ትታ ፈቀቅ በማለት ራስዋን በምታረክስ ጊዜ ያለው የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሚስቱ በእርሱ ላይ እንዳመነዘረችበት ቢጠረጥርና ቅናት ቢያድርበት የሚፈጽመው የሕግ ሥርዓት የሚከተለው ነው፦ ይኸውም ሴትዮዋን በመሠዊያው ፊት ለፊት እንድትቆም ያደርግና ካህኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሥርዓት ይፈጽምባታል፤ ወይም የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢያድርና ሚስቱን ቢጠራጠር ወደ መሠዊያው ፊት አምጥቶአት ካህኑ ይህን የሕግ ሥርዓት ይፈጽምባት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በባልዋ ላይ ለበደለችና ራስዋን ላረከሰች ሴት የቅንዐት ሕግ ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ባልዋን ትታ በረከሰች ጊዜ፥ ወይም በሰው ላይ የቅንዓት መንፈስ በመጣበት ጊዜ፥ ስለ ሚስቱም በቀና ጊዜ፥ የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ ሴቲቱንም በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፥ ካህኑም እንደዚህ ሕግ ሁሉ ያድርግባት። |
በሰይፋችሁ ትመካላችሁ፤ አስጸያፊ ነገሮችን ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት ታረክሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?’
ከበግ ጠጕር ወይም ከበፍታ የተሠራ ልብስ ወይም በሸማኔ ዕቃ የተሠራ ወይም በእጅ የተጠለፈ ጨርቅ ወይም ከቈዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ በደዌ ቢበከል፣ ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለማወቅ ሕጉ ይህ ነው።
ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና።
ካህኑም ሴትዮዋን ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፤ “ሌላ ወንድ ዐብሮሽ ካልተኛ፣ በትዳር ላይ ሆነሽ ወደ ርኩሰት ካላዘነበልሽ ይህ ርግማን የሚያመጣ መራራ ውሃ ጕዳት አያድርስብሽ፤
ወይም አንድ ሰው ሚስቱን ከመጠርጠሩ የተነሣ የቅናት መንፈስ ሲያድርበት በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ ካህኑም ሕጉ በሙሉ በሴቲቱ ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ያድርግ።