La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 5:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና በርግጥም ጐድፋ ብትገኝ ወይም ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና እርሷ ግን ጐድፋ ባትገኝ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርሷም በመርከስዋ ስለ ሚስቱ ቢቀና፤ ወይም እርሷ ሳትረክስ በእርሱ ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ራስዋን ባረከሰች፥ ወይም ራስዋን ሳታረክስ በጥርጣሬ በሚስቱ ላይ የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢመጣ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምስ​ክ​ርም ባይ​ኖ​ር​ባት፥ በም​ን​ዝ​ርም ባት​ያዝ፥ በባ​ል​ዋም ላይ የቅ​ን​ዐት መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ እር​ስ​ዋም ስት​ረ​ክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና ወይም እር​ስዋ ሳት​ረ​ክስ የቅ​ን​ዐቱ መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ ስለ ሚስ​ቱም ቢቀና፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርስዋም ስትረክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና፤ ወይም እርስዋ ሳትረክስ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤ ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥

Ver Capítulo



ዘኍል 5:14
5 Referencias Cruzadas  

ቅናት የባልን ቍጣ ይቀሰቅሳልና፤ በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም።


በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም እንደ መቃብር ጨካኝ ናትና፤ እንደሚንቦገቦግ እሳት፣ እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነድዳለች።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ አሕዛብን ላከማች፣ መንግሥታትን ልሰበስብ፣ መዓቴንና ጽኑ ቍጣዬን በላያቸው ላፈስስ ወስኛለሁ። በቅናቴ ቍጣ እሳት፣ መላዋ ምድር ትቃጠላለችና።


ወይም አንድ ሰው ሚስቱን ከመጠርጠሩ የተነሣ የቅናት መንፈስ ሲያድርበት በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ ካህኑም ሕጉ በሙሉ በሴቲቱ ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ያድርግ።


ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከርሱ እንበልጣለንን?