ዘኍል 36:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አሉ፤ “ምድሪቱን በዕጣ ከፋፍለህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ እንድትሰጣቸው እግዚአብሔር አንተን ጌታዬን ባዘዘ ጊዜ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዝዞሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉ፦ “ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፋፍለህ እንድትሰጣቸው ጌታ አንተን ጌታችንን አዘዘህ፤ ጌታም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አንተን ጌታችንን አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምድሪቱን በዕጣ ለእስራኤል ሕዝብ እንድታከፋፍል እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዞሃል፤ እንዲሁም የዘመዳችንን የጸሎፍሐድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሉም፦ ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፍለህ ትሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዘዘህ፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ትሰጥ ዘንድ አንተን ጌታችንን አዘዘ። |
ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።
ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባል ቢያገቡ ድርሻቸው ከእኛ የዘር ርስት ላይ ተወስዶ የሚያገቧቸው ሰዎች ላሉበት ነገድ ይተላለፋል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በዕጣ ከተደለደለልን ርስት ላይ ከፊሉ ሊቀነስብን ነው።
“ከሊባኖስ እስከ ማስሮን ባለው ተራራማ ምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሲዶናውያንንም ጭምር እኔው ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አሳድጄ አስወጣቸዋለሁ። ብቻ አንተ ባዘዝሁህ መሠረት ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለእስራኤላውያን አካፍል።