ዘኍል 35:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ እንዲሸሽባቸው የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማናቸውም ሰው፥ በስሕተት ሰውን ቢገድል ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ስድስት ከተሞችን ለሌዋውያን ትሰጣላችሁ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞችን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ። |
ከዚያም ከተማውን መካከል በማድረግ ወደ ምሥራቅ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ደቡብ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ምዕራብ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ሰሜን ሁለት ሺሕ ክንድ ከከተማው ውጭ ለካ፤ እነዚህንም ቦታዎች ለከተሞቹ የግጦሽ መሬት ያደርጓቸዋል።
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።
የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሣዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤
ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤