ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።
ዘኍል 33:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም በጕዟቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጕዞም ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ስሞች ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ጻፈ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ተጓዙ የሰፈሩበትን ጻፈ፥ እየተጓዙ ያደሩበት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። |
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።
እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብጻውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ።