ዘኍል 32:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ወደ እርሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ለከብቶቻችን በረቶች፣ ለሴቶቻችንና ለልጆቻችን ከተሞች መሥራት እንወድዳለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እርሱም ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ለበጎቻችን በረቶች ለልጆቻችንም ከተሞች እንሠራለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ወደ ሙሴ ቀርበው እንዲህ አሉ፦ “በመጀመሪያ በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶች፥ ለልጆቻችንም ከተሞችን እንድንሠራ ፍቀድልን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ቀርበው አሉት፥ “በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶችን፥ ለልጆቻችንም ከተሞችን እንሠራለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም ቀርበው አሉት፦ በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶች ለልጆቻችንም ከተሞች እንሠራለን፤ |
ይሁን እንጂ ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ ታጥቀንና በእስራኤላውያን ፊት ግንባር ቀደም ሆነን ለመሄድ ዝግጁ ነን፤ በዚህም ጊዜ ሴቶቻችንና ልጆቻችን በምድሪቱ ላይ ካሉት ነዋሪዎች እንዲጠበቁ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ።
ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤ የአለቃም ድርሻ ለርሱ ተጠብቆለታል። የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፈቃድና፣ በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።”