ዘኍል 31:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያንን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ምድያማውያን ሴቶችንና ሕፃናትን ማረኩ፤ የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ወሰዱ፤ ሀብታቸውን ሁሉ በዘበዙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድያምንም ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና ዕቃቸውን፥ ንብረታቸውንና ኀይላቸውን በዘበዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ። |
ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም ብዙዎቹን ምርኮኞች አድርገው ወደ ደማስቆ ወሰዷቸው። ደግሞም ለእስራኤል ንጉሥ ዐልፎ ተሰጠ፤ እርሱም ከባድ ጕዳት አደረሰበት።
ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፣ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።