ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የእግር ዐልቦዎች፣ የእጅ አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጕትቻዎችና የዐንገት ሐብሎች በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ እንዲሆነን መባ አድርገን ለእግዚአብሔር አምጥተናል።”
ዘኍል 31:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ የተሠራውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ከእነርሱ ወርቁንና በልዩ ልዩ ቅርፅ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴና አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ ተሠርቶ የነበረውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁንና በልዩ ልዩ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ከእጃቸው ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁንና በልዩ ልዩ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ከእጃቸው ተቀበሉ። |
ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የእግር ዐልቦዎች፣ የእጅ አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጕትቻዎችና የዐንገት ሐብሎች በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ እንዲሆነን መባ አድርገን ለእግዚአብሔር አምጥተናል።”
ሙሴና አልዓዛር ከሻለቆቹና ከመቶ አለቆቹ በመቀበል ስጦታ አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀረቡት ወርቅ ዐሥራ ስድስት ሺሕ ሰባት መቶ ዐምሳ ሰቅል መዘነ።