ዘኍል 31:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ላኩ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ወንዶችን መርጣችሁ ወደ ጦርነቱ ላኩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ ብሎ ተናገራቸው። |
ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ምድያማውያንን ለመውጋት እንዲሄዱና ስለ እግዚአብሔርም እንዲበቀሏቸው ከሰዎቻችሁ ጥቂቶቹን ለጦርነት አዘጋጁ።
እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ ዐብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ እስራኤላውያን የገዛ ኀይላቸው እንዳዳናቸው በመቍጠር እንዳይታበዩብኝ፣
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና፤ ወደነዚያ ሸለፈታሞች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን እግዚአብሔርን የሚያግደው የለምና” አለው።