ዘኍል 30:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም ከተሳለች ወይም አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ካስገባች በኋላ ባል ብታገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስእለትም ከተሳለች ወይም ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከአንደበትዋ በችኮላ ከተናገረች በኋላ ባል ብታገባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባል ያላገባች ሴት አስባም ሆነ በግድየለሽነት ስእለት ካደረገች ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል ቃል ከገባች በኋላ ባል ብታገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ባል ያገባች ብትሆን፥ በአንደበቷም እንደ ተናገረች ስለ ራስዋ የተሳለችው ስእለት በራስዋ ላይ ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተሳለችም ጊዜ ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበት ነገር ከአፍዋ በወጣ ጊዜ ባል ያገባች ብትሆን፥ |
ሴቶቹም፣ “ለሰማይዋ ንግሥት በምናጥንበትና የመጠጥ ቍርባን በምናፈስስበት ጊዜ፣ በምስሏ ዕንጐቻ ስንጋግርና የመጠጥ ቍርባን ስናፈስስላት ባሎቻችን አያውቁም ነበርን?” አሉ።
አባቷ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን የትኛውም ስእለቷ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበት መሐላ አይያዝባትም፤ የከለከላት አባቷ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።”