ዘኍል 30:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቷ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን የትኛውም ስእለቷ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበት መሐላ አይያዝባትም፤ የከለከላት አባቷ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና ጌታ ይቅር ይላታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም የሚቃወማት ከሆነ ግን ስእለትዋን የመፈጸም ግዴታ አይኖርባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው አባትዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባቷ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። |
ባሏም ይህንኑ ሰምቶ ምንም ነገር ባይላትና ባይከለክላት ግን ስእለቶቿም ሆኑ ለማድረግ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ የጸኑ ይሆናሉ።
አባቷም መሳሏን ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር፣ ስእለቶቿ በሙሉ፣ ራሷንም ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
ሆኖም ባሏ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን ለመፈጸም የተሳለችውንም ሆነ አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ስለሚያስቀር እግዚአብሔር ከዚህ ነጻ ያደርጋታል።