ዘኍል 30:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏም ይህንኑ ሰምቶ ምንም ነገር ባይላትና ባይከለክላት ግን ስእለቶቿም ሆኑ ለማድረግ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ የጸኑ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልዋም ሰምቶ ዝም ቢላት ባይከለክላትም፥ ስእለትዋ ሁሉ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ካልተቃወማት በቀር ስእለትዋንም ሆነ ከአንድ ነገር ለመከልከል የገባችውን መሐላ መፈጸም ይኖርባታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋም ሰምቶ ዝም ቢላት፥ ባይከለክላትም፥ ስእለቷ ሁሉ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም ሰምቶ ዝም ቢላት ባይከለክላትም፥ ስእለትዋ ሁሉ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። |
ባሏ ሰምቶ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ስእለቶቿንም ሆነ ለማድረግ ቃል የገባቻቸውን ነገሮች የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ባሏ እንዲቀሩ ስላደረጋቸው እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል።
አባቷ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን የትኛውም ስእለቷ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበት መሐላ አይያዝባትም፤ የከለከላት አባቷ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል።