ዘኍል 3:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀዓት ጐሣዎች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀዓትም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀዓትም ወንዶች ልጆች ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ይባሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው እንበረም፥ ይሳዓር፥ ኬብሮን፥ አዛሄል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። |
ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
ከዚያም እነዚሁ ሌዋውያን በሥራው ላይ ተሰማሩ፤ ከቀዓት ዘሮች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፤ ከሜራሪ ዘሮች፣ የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፤ ከጌርሶን ዘሮች፣ የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፤