በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
ዘኍል 3:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቁጠር፤ ወንዱን ሁሉ ዕድሜው አንድ ወር የሞላውንና ከዚያም በላይ ያለውን ቁጠራቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሌዋውያንን በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው መድበህ ቊጠር፤ ከተወለደ አንድ ወር የሞላውንና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ቊጠር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው። |
በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
“ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣ በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣ እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።
በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤
አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺሕ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ ዐብረዋቸው አልተቈጠሩም።
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተቈጠሩት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው ስምንት ሺሕ ስድስት መቶ ሲሆን፣ ቀዓታውያንም መቅደሱን የመጠበቅ ኀላፊነት ነበራቸው።
ኢየሱስም ይህን ሲያይ ተቈጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።