La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 26:59 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርሷ በግብጽ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የቆሬ ወገን፥ የቀ​ዓት ወገን። ቀዓ​ትም እን​በ​ረ​ምን ወለደ። በግ​ብፅ ሀገር እነ​ዚ​ህን ሌዋ​ው​ያ​ንን የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጅ የእ​ን​በ​ረም ሚስት ስም ዮካ​ብድ ነበረ። ለእ​ን​በ​ረ​ምም አሮ​ን​ንና ሙሴን እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

Ver Capítulo



ዘኍል 26:59
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም የአሮን እኅት ነቢዪቱ ማርያም ከበሮዋን አንሥታ ያዘች፤ የቀሩትም ሴቶች ሁሉ ከበሮ ይዘው እያሸበሸቡ ተከተሏት።


የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ታይ ነበር።


እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።


“ ‘ከአባትህ እኅት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።


ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር።


በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ተቀመጡ፤ እዚያ ማርያም ሞተች፤ ተቀበረችም።