ዘኍል 26:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የአሴር ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የአሴር ተወላጆች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰምዒያውያን ወገኖች ሁሉ ቍጥራቸው ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የአሴር ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። |