ዘኍል 26:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በዪምና በኩል፣ የዪምናውያን ጐሣ፣ በየሱዊ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የአሴር ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሴር ነገድ ተወላጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ በሪዓ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበዓሌም ልጆች አዴርና ኖሐማን፤ ከአዴር የአዴራውያን ወገን፥ ከኖሐማን የኖሐማናውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። |
ከአሴር ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።