ዘኍል 26:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሱቱላ ልጅ፦ ዔራንና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሲማኤር የሲማኤራውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን። |
የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣ በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤
እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።