ዘኍል 26:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው፤ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስምዖን ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ኻያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው፤ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። |
የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤ በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤ በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤