ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚያች ዕለት ጧት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ።
ዘኍል 25:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺሕ ደርሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅሠፍትም የሞተው ሰው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እስከዚያው ሰዓት ድረስ ያ መቅሠፍት ኻያ አራት ሺህ ሕዝብ አጥፍቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅሠፍቱም የሞቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅሠፍትም የሞተው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። |
ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚያች ዕለት ጧት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ።
የበለዓምን ምክር ተቀብለው በፌጎር በተፈጸመው ድርጊት እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር እንዲመለሱና የእግዚአብሔርም ሕዝብ እንዲቀሠፍ ያደረጉት እነርሱ ናቸው።