ዘኍል 24:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤ ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤ ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤ በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከግብፅ መርቶ አውጥቶታል፤ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር አለው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፤ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፤ በፍላጾቹም ጠላቱን ይወጋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከግብፅ አውጥቶታል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል። |
“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣ የተበተነ መንጋ ነው፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ ቦጫጭቆ በላው፤ በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”
የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።
በንጉሡ ትእዛዝ፣ ዳንኤልን በሐሰት የከሰሱትን ሰዎች፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ አምጥተው፣ በአንበሶቹ ጕድጓድ ውስጥ ጣሏቸው፤ ገና ወደ ጕድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱም፣ አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”
በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ተነሥተው፣ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ! ውሃ የለ! ይህን የማይረባ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል” ሲሉ ተናገሩ።
በዚያም ሄሮድስ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ኖረ። በዚህም፣ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት” በማለት ጌታ በነቢዩ አንደበት የተናገረው ቃል ተፈጸመ።
አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህና ብዙዎችን ከአንተ የሚበልጡ ታላላቆችና ብርቱዎች የሆኑትን ሰባቱን አሕዛብ፦ ኬጢያውያንን፤ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ በሚያስወጣቸው ጊዜ፣
ከግብጽ በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ፣ እናንተም ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ፈጽሞ ያጠፋችኋቸውን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት፣ ሴዎንንና ዐግን ምን እንዳደረጋችኋቸው ሰምተናል።