ዘኍል 20:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሙሴ ልክ እንደ ታዘዘው በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከጌታ ፊት ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከድንኳኑ ውስጥ በትሩን አመጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የነበረችውን በትሩን ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። |
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጕረምረም ይህ ይገታዋል” አለው።