ዘኍል 19:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ እየተመለከተም ጊደሯን ያቃጥሏት፤ ቈዳዋም፣ ሥጋዋም፣ ደሟም፣ ፈርሷም ጭምር ይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጊደሪቱም በፊቱ ትቃጠላለች፤ ቁርበትዋም ሥጋዋም ደምዋም ፈርስዋም ይቃጠላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንስሳዪቱ በሙሉ ማለትም ቆዳዋ፥ ሥጋዋ፥ ደምዋና የሆድ ዕቃዋ ሁሉ በካህኑ ፊት ይቃጠል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጊደሪቱንም በፊቱ ያቃጥሏታል፤ ቍርበቷንም፥ ሥጋዋንም፥ ደምዋንም፥ ፈርስዋንም ያቃጥሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጊደሪቱም በፊቱ ትቃጠላለች፤ ቁርበትዋም ሥጋዋም ደምዋም ፈርስዋም ይቃጠላል። |
መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ወይፈኑንም ከሰፈር ውጭ ያውጣው፤ የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለው ሁሉ ይህኛውንም ያቃጥል፤ ይህም ስለ ሕዝቡ የሚቀርብ የኀጢአት መሥዋዕት ነው።