እነርሱ እየገደሉ እኔም ብቻዬን ሳለሁ፣ በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን አውርደህ የእስራኤልን ቅሬታዎች ሁሉ ልታጠፋ ነውን?” በማለት ጮኽሁ።
ዘኍል 16:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ይህን ሲሰማ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግምባሩ ወድቆ ሰገደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ይህን በሰማ ጊዜ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግንባሩ ወደቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግምባሩ ወደቀ፤ |
እነርሱ እየገደሉ እኔም ብቻዬን ሳለሁ፣ በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን አውርደህ የእስራኤልን ቅሬታዎች ሁሉ ልታጠፋ ነውን?” በማለት ጮኽሁ።
ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።
ቆሬንና ተከታዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ “የርሱ የሆነውና የተቀደሰው ማን መሆኑን እግዚአብሔር ጧት ያሳውቃል፤ ወደ ራሱም ያመጣዋል፤ የሚመርጠውን ሰው ወደ ራሱ እንዲቀርብ ያደርገዋል።
በዚህ ጊዜ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፤ በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፋ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም እንደዚሁ አደረጉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።