“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ዘኍል 14:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በዚያ ያጋጥሟችኋልና። እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁትና እርሱም ከእናንተ ጋራ ስለማይሆን በሰይፍ ትወድቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ ጌታን ከመከተል ተመልሳችኋልና ጌታ ከእናንተ ጋር አይሆንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐማሌቃውያንንና ከነዓናውያንን ፊት ለፊት ባያችሁ ጊዜ በጦርነት ትሞታላችሁ፤ እርሱን መከተል እምቢ ስላላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋራ ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል።
አማሌቃውያን የሚኖሩት በኔጌብ፣ ኬጢያውያን ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በኰረብታማው አገር፣ ከነዓናውያን የሚኖሩት ደግሞ በባሕሩ አቅራቢያና በዮርዳኖስ ዳርቻ ነው።”
እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ።
እንግዲህ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ለመቋቋም ያልቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። ጀርባቸውን አዙረው የሸሹትም ለጥፋት በመዳረጋቸው ነው። ዕርም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ፣ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋራ አልሆንም።
እርሷም፣ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም ነበር።