የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
ዘኍል 14:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለ ተከተለኝ እርሱ ሄዶ ወደ ነበረበት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አገልጋዬ ካሌብ ልዩ አመለካከት ስላለውና ለእኔ ያለውንም ታማኝነት ስላጸና ሄዶ የመረመራትን ምድር እሰጠዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል። |
የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ለእግዚአብሔር ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።
ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።”