ዘኍል 13:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ካሌብ ሕዝቡን በሙሴ ፊት ጸጥ አሠኝቶ፣ “እንውጣ! ምድራቸውን እንውረስ፤ ማሸነፍም እንችላለን” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ “ማሸነፍ እንችላለንና እንውጣ፥ እንውረሰው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፥ “አይደለም! ማሸነፍን እንችላለንና እንውጣ፤ እንውረሳት” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ። |
አማሌቃውያን የሚኖሩት በኔጌብ፣ ኬጢያውያን ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በኰረብታማው አገር፣ ከነዓናውያን የሚኖሩት ደግሞ በባሕሩ አቅራቢያና በዮርዳኖስ ዳርቻ ነው።”
አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል።