ዘኍል 1:54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ይህን ሁሉ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆችም እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ፤ እንዲሁ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ። |
በዚህ መሠረት የማደሪያው ድንኳን፣ የመገናኛው ድንኳን ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ። እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉን ነገር ሠሩ።
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነ ወንዶች ስማቸው አንድ በአንድ ተመዘገበ። እንዲህ አድርጎም በሲና ምድረ በዳ ቈጠራቸው።
ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።”
ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።
እነርሱም በመጀመሪያው ወር፣ በዐሥራ አራተኛውም ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካ አደረጉ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉንም አደረጉ።
ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር፣ በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።