ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
ዘኍል 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቁጠሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጡትን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቍጠሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጡትን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቍጠሩአቸው። |
ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሯቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰይፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው።
አሜስያስ የይሁዳን ሕዝብ በአንድነት ሰብስቦ፣ እንደየቤተ ሰቡ በሻለቆችና በመቶ አለቆች በመደልደል በመላው ይሁዳና በብንያም መደባቸው። ከዚያም ዕድሜያቸው ሃያና ከሃያ በላይ የሆናቸውን ሰብስቦ፣ ለውትድርና አገልግሎት ብቁ ሆነው ጋሻና ጦር መያዝ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺሕ ሰዎች አገኘ።
“የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ሰራዊታችሁን ከግብጽ ምድር ያወጣሁት በዚች ዕለት ነውና። ይህን ዕለት ለሚቀጥለው ትውልድ ቋሚ ሥርዐት በማድረግ አክብሩት።
ከተቈጠሩት ጋራ ዐብረው ከሆኑት ሃያና ከሃያ ዓመት በላይ የሆናቸው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ሰዎች የሰጡት እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም ግማሽ ሰቅል ነበረ።
“ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።”
‘በፍጹም ልባቸው ስላልተከተሉኝ ከግብጽ ከወጡት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም፤
አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፣ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ ቤቱ ይቈይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
በዚያ ጊዜ እኔ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ለእናንተ ሰጥቷችኋል፤ ይሁን እንጂ የአካል ብቃት ያላቸው ሰዎቻችሁ ሁሉ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ፊት በመቅደም መሻገር አለባቸው።