ነህምያ 11:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በራሳቸው ፈቃድ የተነሣሡትን ሰዎች ሁሉ አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በፈቃደኝነት ራሳቸውን የሰጡትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር የበጎ ፈቃድ ዝንባሌ ያለውን ሰው ሁሉ አመሰገነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ። |
ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቈጠርልሃል።