በርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል።
ማቴዎስ 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል።’” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ራስህን ወደ ታች ወርውር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እግሮችህ በድንጋይ እንዳይሰናከሉ፥ በእጆቻቸው ይደግፉህ ዘንድ መላእክቱን ያዝልሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ ከዚህ ወደታች ራስህን ወርውር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው። |
በርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል።