ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ ዐብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ዐሳረፉ፤ አብያታርም ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቅቆ እስኪወጣ ድረስ መሥዋዕት አቀረበ።
ማርቆስ 2:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሊቀ ካህናቱ በአብያታር ዘመን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ለርሱም ሆነ ዐብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብያታር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብያታር የካህናት አለቃ በነበረበት ዘመን እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፥ ከካህናት በቀር ለሌሎች መብላት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰውን የመባ ኅብስት በላ፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሰዎች ሰጣቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው። |
ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ ዐብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ዐሳረፉ፤ አብያታርም ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቅቆ እስኪወጣ ድረስ መሥዋዕት አቀረበ።
ንጉሥ ሰሎሞንም እናቱን፣ “ስለ ምን ሱነማዪቱን አቢሳን ብቻ ለአዶንያስ ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ስለ ሆነ መንግሥቱንም ጠይቂለት እንጂ፤ ለርሱ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም ለካህኑ ለአብያታርና ለጽሩያ ልጅ ለኢዮአብ ጠይቂላቸው” አላት።
የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቢሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው።
ዳዊትም ካህኑ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ኖብ ሄደ። አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፣ “ምነው ብቻህን? ሰውስ ለምን ዐብሮህ የለም?” ሲል ጠየቀው።