ሉቃስ 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ ወሰዱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወሰዱትና በጲላጦስ ፊት አቀረቡት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም በሞላው ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና፦ |
በእውነትም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋራ በዚህች ከተማ አንተ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለማሤር ተሰበሰቡ፤