በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ሉቃስ 1:50 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሕረቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ በሚፈሩት ላይ ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቅርታውም ለሚፈሩት ለልጅ ልጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። |
በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።