ዘሌዋውያን 7:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ማንኛውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበው ካህን ቈዳውን ለራሱ ይውሰድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የማናቸውንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ካህን፥ ያቀረበው የሚቃጠለው መሥዋዕት ቆዳ ለዚያው ካህን ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረበው እንስሳ፥ ቆዳው ተገፎ መሥዋዕቱን ላቀረበው ካህን ይሰጠዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውን የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ካህን ያቀረበው የሚቃጠለው መሥዋዕት ቍርበት ለዚያው ካህን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማናቸውንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ካህን ያቀረበው የሚቃጠለው መሥዋዕት ቁርበት ለዚያው ካህን ይሆናል። |