ዘሌዋውያን 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህል ቍርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ቂጣ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ እርሾ ያልገባበት፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መባው በምጣድ የተጋገረ ኅብስት ከሆነ እርሾ ሳይነካው የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍርባንህም በምጣድ የተጋገረ ቍርባን ቢሆን፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ስንዴ ዱቄት ቂጣ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን። |
“ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ።
ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣