Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 2:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ ‘በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ የእህል ቍርባን በምታቀርብበት ጊዜ፣ ከላመ ዱቄት ተዘጋጅቶ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ኅብስት ይሁን፤ አለዚያም ያለ እርሾ በሥሡ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “በምድጃ የተጋገረውን የእህል ቁርባን ስታቀርብ በዘይት ተለውሶ እርሾ ያልገባበት፥ የመልካም ዱቄት የቂጣ እንጐቻ ወይም እርሾ ያልነካው በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 መባው በምድጃ የተጋገረ ከሆነም እርሾ ያልነካው ይሁን፤ እርሱም የወይራ ዘይት ተደባልቆበት ከላመ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ ወይም በዘይት የታሸ ቂጣ መሆን አለበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረ​ውን ቍር​ባን ስታ​ቀ​ርብ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት፥ የቂጣ እን​ጎቻ ወይም በዘ​ይት የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእቶን የተጋገረውን የእህል ቍርባን ስታቀርብ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የቂጣ እንጐቻ ወይም በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 2:4
21 Referencias Cruzadas  

እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።


ሥጋውንም በዚያችው ሌሊት በእሳት ላይ ጠብሰው ከመራራ ቅጠልና ከቂጣ ጋራ ይብሉት።


የእስራኤልም ሕዝብ ምግቡን መና አሉት፤ እርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣሙም ከማር እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበር።


እርሾ ከሌለው ከምርጥ የስንዴ ዱቄት ቂጣ፣ በዘይት የተለወሰ የቂጣ ዕንጐቻና በዘይት የተቀባ ኅብስት ጋግር።


“እነሆ፤ ደግፌ የያዝሁት፣ በርሱም ደስ የሚለኝ የመረጥሁት አገልጋዬ፤ መንፈሴን በርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


እርሱም፣ “ይህ ስፍራ ሕዝቡን ለመቀደስ መሥዋዕቱን ወደ ውጩ አደባባይ እንዳያወጡ፣ ካህናቱ የበደሉን መሥዋዕትና የኀጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፣ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ቦታ ነው” አለኝ።


የሚቀርበውን መሥዋዕት ከመሠዊያው በስተሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ካህናቱ የአሮን ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ሁሉ ይርጩት።


ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ቂጣ ጋግሩ፤ እጅግ ቅዱስ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።


ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቍርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው።


“ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ።


ከእነዚህም ጋራ የሚቀርበውን የእህልና የመጠጥ ቍርባን ቂጣ ማለት ከላመ ዱቄት በዘይት የተለወሱ ዕንጐቻዎች እንዲሁም በሥሡ የተጋገረና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ያምጣ።


ከዚያም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዝናለች፤ እዚሁ ሁኑና ከእኔ ጋራ ነቅታችሁ ቈዩ” አላቸው።


“አሁንስ ነፍሴ ተጨነቀች፤ ምን ልበል? አባት ሆይ፤ ከዚህች ሰዓት ብታድነኝስ? ይሁን፤ የመጣሁት ለዚህች ሰዓት ነውና።


እግዚአብሔር መንፈሱን ሳይሰፍር ስለሚሰጥ፣ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል።


እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።


እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፣ ማታለልን ሁሉ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።


“እርሱ ኀጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos